Fana: At a Speed of Life!

ዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን አንድነት፣ ቁርጠኝነትና አይበገሬነት መገለጫ ነው – አቶ ሃይሉ አዱኛ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የአንድነት፣ ቁርጠኝነትና አይበገሬነት መገለጫ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ፡፡

49ኛው የጉሚ በለል መድረክ “ዓድዋ የጋራ ድል የወል ትውስታ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ሃይሉ አዱኛ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የዓድዋ ድል የቅኝ ገዥነትን አስተሳሰብ በመስበር ለሰው ልጆች እኩልነት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ብለዋል፡፡

በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ቀደምት አባቶች በከፈሉት ውድ መስዋዕትነት ነጻነቷ እና ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ መቆየቱን አውስተዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ተምሳሌት መሆኗን ጠቅሰው ÷ ጀግንነት ከተንጸባረቀባቸው የጦርነት አውድማዎች ዓድዋ ግንባር ቀደም መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች እና የተለያዩ ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.