የመራጮች ምዝገባ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል፡፡
የመራጮች ምዝገባ መጀመሩን ተከትሎም በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ዜጎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ
የምርጫ ካርዳቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡
በምዝገባ ሒደቱ 18 ዓመት የሞላው ኢትዮጵያዊ፣ በአካባቢው 6 ወር የኖረና በልዩ ሁኔታ ምርጫ ያልተከለከለ ዜጋ ሁሉ መሳተፍ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
ምዝገባው ከየካቲት 28 ጀምሮ እስከ መጋቢት 1 ቀን ድረስ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚከናወን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመላክታል፡፡
በቦርዱ ከተመዘገቡ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች 10 ሺህ 934 እጩዎች የቀረቡ ሲሆን ÷ 2 ሺህ 98 ዕጩዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ 8 ሺህ 736 ደግሞ የክልል ተወካዮች ናቸው፡፡