በሩሲያ በደረሰ የወታደራዊ አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን በክሪሚያ ግዛት ተከስክሶ ሁሉም ተሳፋሪዎች እና የበረራ ሰራተኞች ሕይውት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ ኤኤን-26 የተባለው ወታደራዊ አውሮፕላኑ 23 ተሳፋሪዎችን እና 6 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ ነበር፡፡
አውሮፕላኑ በክሪሚያ ግዛት እያለፈ በነበረበት ወቅት የግንኙነት መስመሩ መቋረጡን የገለፀው ሚኒስቴሩ÷ በኋላ ላይ ም መከስከሱ መታወቁን ገልጿል።
በአካባቢው የተሰማራው የነፍስ አድን ቡድን በአደጋው ሁሉም ተሳፋሪዎች እና የበረራ ሰራተኞች ህይወት ማለፉን አረጋግጧል።
አውሮፕላኑ በአለታማ ስፍራ መከሰከሱ አደጋውን የከፋ እንዲሆን ማድረጉ ነው የተገለፀው፡፡
የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የሩሲያ ባለስልጣናት በአካባቢው ምርመራ ጀምረዋል መባሉን ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል፡፡
በሚኪያስ አየለ