Fana: At a Speed of Life!

የኢራን አብዮታዊ ዘብ የደህንነት ሹም ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2018 (ኤፍኤምሲ) የኢራን አብዮታዊ ዘብ የደህንነት ሹም ሜጀር ጀኔራል መጂድ ኻደሚ በአሜሪካና በእስራኤል ጥምር ጥቃት በዛሬው ዕለት መገደላቸውን ኢራን አስታውቃለች።

የአብዮታዊ ዘቡ ባወጣው መግለጫ በደህንነት ሹሙ ላይ የተፈጸመው ግድያ በማውገዝ፤ ድርጊቱን በአሜሪካ እና እስራኤል የተፈጸመ የሽብር ጥቃት ብሎታል።

ኢራን ጥቃቱን በመፈጸም አሜሪካ እና እስራኤልን ተጠያቂ ስታደርግ፤ እስራኤል በበኩሏ ጀኔራል ኻደሚን እና ሌላ አንድ ከፍተኛ መኮንን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈጸሟን ይፋ በማድረግ ኃላፊነቱን ወስዳለች።

ሜጀር ጄኔራል መጂድ ኻደሚ ወደ ኃላፊነት የመጡት ከእሳቸው በፊት የደህንነት ሹም የነበሩት መሐመድ ካዘሚ በፈረንጆቹ 2025 በሰኔ ወር ላይ በነበረው የ12 ቀናት ጦርነት በተመሳሳይ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ነበር።

የደህንነት ሹሙ መገደል በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ከፍተኛ ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል የተለያዩ ዘገባዎች ጠቁመዋል።

የአብዮታዊ ዘቡ የደህንነት ክንፍ በኢራን ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያለውና ለሀገሪቱ የበላይ መሪ ቀጥታ ሪፖርት የሚያደርግ ተቋም ነው።

በሶስና አለማየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.