Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከር…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በ400 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በከተማዋ ኢንዱስትሪ መንደር ቁጥር 4 በግል ባለሃብት የተገነባው የምግብ ዘይት ፋብሪካ በቀን 20 ሺህ ሊትር ዘይት የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ፋብሪካውን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ተፈሪ ታረቀኝ  እና የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኛው በጋራ መርቀውታል።

የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ግርማይ ልጅዓለም በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በከተማዋ በዚህ ዓመት 20 መካከለኛና ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው።

የዘይት ፋብሪካው የወቅቱን የዘይት አቅርቦት እጥረት ከመፍታት ባለፈ ገበያውን ለማረጋጋት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

የፋብሪካው ባለቤት አቶ አደራጀው ገብረሚካኤል በበኩላቸው ፋብሪካው ባለፉት አራት ወራት በሙከራ ደረጃ ዘይት እያመረተ መቆየቱን ገልጸው÷ በሙሉ አቅም ወደ ስራ ሲገባ ለ130 ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.