Fana: At a Speed of Life!

ዘመኑን የዋጁ የጨቅላ ሕጻናት ጽኑ ሕሙማን ማዕከላትን ለማስፋፋት…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘመኑን የዋጁ የጨቅላ ሕጻናት ጽኑ ሕሙማን ማዕከላትን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፡፡

በሆስፒታሉ በ27 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ወጪ በዘመናዊ መልኩ እድሳት የተደረገለት የጨቅላ ሕጻናት ጽኑ ሕሙማን ሕክምና ማዕከል ተመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌን (ዶ/ር) ጨምሮ የሆስፒታሉ አመራሮች እና የአጋር አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የጨቅላ ሕጻናት ጽኑ ሕሙማን ሕክምናና ክብካቤ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ለማስፋፋት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በሆስፒታሉ እድሳት የተደረገለት የጨቅላ ሕጻናት ጽኑ ሕሙማን ሕክምና ማዕከል የሕጻናትና እናቶችን ሕክምና አገልግሎትን ጥራት ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡

በተለይም በጨቅላ ሕጻናት ጽኑ ሕሙማን ሕክምና ክፍል ውስጥ በተለያዩ የሕክምና ግብዓቶች እጥረት ሊፈጠር የሚችልን ኢንፌክሽን ለማስቀረት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተጠቅሷል፡፡

እድሳቱ የውሃ ችግርን ከመቅረፍና የኦክስጅን አቅርቦትን ከማሟላት ባለፈ የተሳለጠ ሕክምና እንዲኖር የሚያስችሉ ግንባታዎች መከናወናቸው ተጠቁሟል፡፡

የማዕከሉን እድሳት ከኢጣሊያን ኮኦፕሬሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ዶክተርስ ዊዝ አፍሪካ ኩአም ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው ያከናወነው፡፡

በፕሮጀክቱ ከእድሳቱ በተጨማሪ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ እና የባለሙያ ሥልጠና መሰጠቱ ተመላክቷል፡፡
ዶተርስ ዊዝ አፍሪካ ኩአም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ÷ በኢትዮጵያ በሶማሌ፣ ትግራይ፣ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች ከ20 በላይ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.