Fana: At a Speed of Life!

አርበኝነት በእውቀት ጎዳና መመራት ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አርበኝነት በእውቀት ጎዳና መመራት ነው አሉ።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት 85ኛው የአርበኞች ቀን በአዲስ አበባ አራት ኪሎ የአርበኞች መታሰቢያ ሐውልት እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞ ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ ጀግኖች አርበኞች፣ የአርበኛ ቤተሰቦች እና የመዲናዋ ነዋሪዎች በስፍራው ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሰላም፣ ነፃነት እና በራስ መተማመን ማንም የማይነጥቀን ኖረን የያዝነው የራሳችን ሐብት ነው ብለዋል።

ጀግንነት የሰከነና ለሀገር የሚታበኑበት ጸጋ መሆኑን ገልጸው፤ በላባቸው፣ በደማችው፣ በሙያቸውና በእውቀታቸው ሀገርን የሚያገለግሉ የዘመኑ አርበኞች እንደሆኑ አስገንዝበዋል።

በጥፋት መስመር ላይ የተሰማሩ ወደልማት መስመር እንዲመለሱም ጥሪ አቅርበዋል።

ሀሰትን፣ ውስልትንና ቅጥፈት የማይፀየፍ ትውልድ ከአርበኝነህ እንደሚርቅ አስረድተው፤ አርበኝነት በእውቀት ጎዳና መመራት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አርበኝነት የዕድሜ ልክ መታመን ውጤት መሆኑንም አፅንዖት በመስጠት አንስተዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.