Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካዊያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የጉለሌ እንጀራ ማምረቻን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‌‌‎አፍሪካዊያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ የጉለሌ እንጀራ ማምረቻን ጎብኝተዋል።

የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የተሰሩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ለብዙ እናቶች የስራ እድል የፈጠረውን የጉለሌ እንጀራ ማምረቻ ማዕከልን ጎበኝተዋል።

ተጽዕኖ ፈጣሪዎቹ በማዕከሉ ተወዳጅ የኢትዮጵያን ምግብ የሆነውን እንጀራ የመጋገር ሂደትን ለመመልከት ዕድል አግኝተዋል።

ይህም በዲጂታል መድረኮች ላይ የኢትዮጵያን ባሕል እና የምግብ ስርዓትን በስፋት ለማስተዋወቅ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.