Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።

‎በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረጉ ቁልፍ ስምምነቶች ልውውጥን በጋራ መምራታቸውን ገልጸዋል።

በዚሁም የታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ የብድር ስምምነት እና የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ልውውጥ ይገኙበታል ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.