Fana: At a Speed of Life!

የመቐለ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ለነዋሪዎች የተሻለ የኑሮ አካባቢ ለመፍጠር ወሳኝ ሚና አለው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመቐለ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ለነዋሪዎች የተሻለ የኑሮ አካባቢ ለመፍጠርና ኢኮኖሚያዊ አቅምን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና አለው አሉ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር)
የመቐለ ከተማ ባለአደራ አስተዳደር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክትን በተመለከተ ከከተማዋ ክፍለ ከተሞች አመራሮች ጋር የመጀመሪያ ዙር ውይይት አካሂዷል።
የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ የከተማዋን ውበትና ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የልማት ስራው የነዋሪዎችን ፍላጎትና ተጠቃሚነት ባማከለ መልኩ መከናወን አለበት፡፡
ፕሮጀክቱ የታለመለትን ውጤት እንዲያስመዘግብ የክፍለ ከተሞች አመራሮች በተቀናጀ አመራር መሥራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡
ወጣቶችን በልማት ሥራው በማሳተፍ የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የግል ዘርፉንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማሳተፍ ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባም አፅንዖት ሰጥተዋል።
የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ የከተማዋን ገጽታ ከማሻሻል ባለፈ የሕዝብ አገልግሎት አውታሮችን በማዘመን፣ የንግድና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በማጠናከር፣ ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠርና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማበረታታት ረገድ በሚኖረው ፋይዳ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በግዛቸው ግርማዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.