Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ ዴሞክራሲን ለማጽናትና ቅቡልነት ያለውን መንግሥት ለመመስረት ወሳኝ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምርጫ ዴሞክራሲን ለማጽናትና ቅቡልነት ያለውን መንግሥት ለመመስረት ወሳኝ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሕርዳር ምርጫ ክልል ህዳሴ ምርጫ ጣቢያ (02-1) ተገኝተው ድምፃቸውን በሰጡበት ወቅት÷ ሕዝቡ በምርጫ ያደረገው ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ምርጫ ዲዴሞክራሲን ለማጽናትና ቅቡልነት ያለውን መንግሥት ለመመስረት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምንም ብልጽግና ፓርቲም ይሁን እርሳቸው በጸጋ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

የሀገር መቀጠል እንጂ የፓርቲ መቀጠል ዋነኛው አጀንዳ ሊሆን አይገባም ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

በአቤል ነዋይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.