መንግሥት የሚመሰረተው በሕዝብ ድምፅ ብቻ ነው – ዕጩ ተወዳዳሪዎች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት የሚመሰረተው በጠመንጃ ሳይሆን በሕዝብ ድምፅ ብቻ ነው አሉ በኮምቦልቻ ከተማ በቃሉ አንድ ምርጫ ክልል የሚወዳደሩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ዕጩ እና የግል ተወዳዳሪዎች።
ዕጩ ተወዳዳሪዎቹ በሰጡት አስተያየት እንዳሉት÷ በምርጫ ክልሉ እየተካሄደ ያለው የምርጫ ሂደት ሰላማዊና ፍትሐዊ ነው።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ይማም በላይ ምርጫው በዴሞክራሲያዊ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ኑርየ እብሬ በበኩላቸው÷ በማኅበረሰቡ እየታየ ያለው የምርጫ ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ በንቃት እየተሳተፈ መሆኑን መመልከታቸውን የገለጹት ደግሞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል ተወዳዳሪ እጩ ሀሰን ይመር (ዶ/ር) ናቸው።
በአለባቸው አባተ