Fana: At a Speed of Life!

በአራት ክልሎች የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሶማሌና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ከ418 ሺህ በላይ ህፃናት ለማድረስ ታቅዶ እየተሰጠ ነው።

በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክትባት የምንከላከላቸው በሽታዎች ቅኝት ምላሽ ሰጪ ባለሙያ ታደሰ ያለው እንዳሉት÷ ክትባትን በመጠቀም የበለፀገና ጤናው የተጠበቀ ዜጋ ለመፍጠር እየተሰራ ይገኛል።

በዚህም በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሶማሌና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠት መጀመሩን ተናግረዋል።

በሚሰጠው ክትባትም 418 ሺህ 569 ህፃናትን ለማድረስ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸው÷ ክትባቱ በትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት፣ ቤት ለቤትና ህጻናት በሚገኙበት አካባቢ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ማሕበረሰቡም በአካባቢያቸው የሚገኙ ህፃናትን በማስከተብ ከበሽታው ለመጠበቅ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ እንዳለበት ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.