Fana: At a Speed of Life!

ተፈናቃዮችና በካምፕ የሚኖሩ ወታደሮች በዛሬው እለት ድምጻቸውን ሰጥተዋል – ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመከላከያ ካምፖችና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት የተካሄደው የድምጽ መስጠት ሒደት ተጠናቅቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ በሰጡት መግለጫ፥ በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሒደት ተፈናቃዮችና በካምፕ የሚኖሩ ወታደሮች ድምጽ መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡

በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች በተደረገው የድምፅ መስጠት ሒደት በ442 ወታደራዊ ካምፖች እና በ82 የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ምርጫ መካሄዱን ነው ያመላከቱት።

በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን በወቅቱ የማድረስና የመራጮች ትምህርት የመስጠት ስራዎች ቀድመው መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

በሄብሮን ዋልታው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.