ፋና ላምሮት በፍጻሜ ዋዜማ በነገው ዕለት ቀጥሎ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ላለፉት 11 ሳምንታት በጠንካራ ፉክክር የቆየው የፋና ላምሮት የምዕራፍ 22 የፍጻሜ ዋዜማ ውድድር በነገው ዕለት ይካሄዳል።
አምስቱ የቅዳሜ ተወዳዳሪዎች ዳንኤል አለልኝ፣ ኤርሚያስ መንግስቴ፣ ኤልያስ ገዛኸኝ፣ የአብሥራ ገዛኸኝ እና ቃለአብ ገዛኸኝ ከኮከብ ባንድ ጋር ለፍጻሜ ለማለፍ ይፋለማሉ፡፡
በምዕራፉ ፍጻሜ የሚቀሩ 4 ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል፤ እነማን ወደ ፍጻሜው ያልፉ ይሆን?
ለፍጻሜ የሚደርሱ አራት ተወዳዳሪዎች ወደ 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል፡፡
የፋና ላምሮት የምዕራፍ 22 የፍጻሜ ዋዜማ ውድድርን በቀጥታ ስርጭት ነገ ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ይጠብቁን፡፡
በለምለም ዮሐንስ