በፋና 80 ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ወሳኝ ፍልሚያ ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና 80 የውዝዋዜና ዳንስ ውድድር በምዕራፍ 5 ምድብ ሁለት 8ኛ ሳምንት ውድድሩን ለማድመቅ ተመልሷል።
በዚህ ሳምንት 5 የዳንስ ቡድኖች ወደ መድረኩ የሚቀርቡ ሲሆን÷ የትኞቹ ቡድኖች በውድድሩ እንደሚቆዩና የትኛው ቡድን ከውድድሩ እንደሚሰናበት በጉጉት ይጠበቃል።
ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለመቀላቀል በሚደረገው በዚህ ወሳኝ ፍልሚያ የባሕልና የዘመናዊ ዳንስ ቡድኖች የዳኞችንና የተመልካቾችን ልብ ለመማረክ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
በውድድሩ የሚሳተፉት ኢትዮ ኪንግ እና ጃኖ ዘመናዊ ዳንስ ቡድኖች እንዲሁም አፍሮ፣ ኤዞፕ እና ዮዳሄ የባሕል ቡድኖች ናቸው።
ከአምስቱ ቡድኖች መካከል የትኞቹ ወደ ቀጣዩ የውድድር ምዕራፍ እንደሚያልፉና የትኛው ቡድን የውድድር ጉዞውን እንደሚያበቃ በዚህ ሳምንት ይለያል።
የፋና 80 የውዝዋዜና ዳንስ ውድድር 8ኛ ሳምንት ውድድር እሑድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥንና በፋና ፕላስ ይጠብቁን።
በብርኽቲ ማህተም