የቢሾፍቱ አቡሴራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ…
👉ፕሮጀክቱ በግንባታው ወቅት በሺህ የሚቆጠሩ መሃንዲሶችንና ሰራተኞችን ቀጥሮ እያሰራ ያለ ሲሆን÷ ሥራ ሲጀምር ደግሞ በአየር መንገዱ፣ በሆቴሎችና በሎጂስቲክስ ዘርፍ ለበርካታ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራል።
👉ይህ ሜጋ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 12 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን ÷ ለቦታው መሬት ማስተካከል እና የዝግጅት ሥራዎች 610 ሚሊየን ዶላር ተመድቦ ሥራው በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።
👉የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በፈረንጆቹ እስከ 2030 ድረስ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል፤
👉የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ በዓመት 60 ሚሊዮን፣ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ደግሞ እስከ 110 ሚሊየን መንገደኞችን የማስተናገድ ግዙፍ አቅም ይኖረዋል።
👉ለቀጣዩ ትውልድ ኩራት የሚሆኑ ዘላቂ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ያረጋግጣል፤
👉በውስጡ ዘመናዊ ሆቴሎችን፣ የገበያ ማዕከላትን፣ የንግድና የዕቃ መጋዘን (Cargo) ኮምፕሌክሶችን ያካትታል። አዲሱ አየር ማረፊያ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በፈጣን የኤክስፕረስ መንገድ እና በከፍተኛ ፍጥነት ተንቀሳቃሽ የባቡር መስመር እንደሚገናኝ ይጠበቃል፡፡
👉የኢትዮጵያን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እድገት ሀገሪቱን ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን ዘላቂ ሞተር ይሆናል።
👉በዓመት እስከ 110 ሚሊየን መንገደኞችን በማስተናገድ ከትራንዚት፣ ከቀረጥ ነፃ ንግድ እና ከአየር መንገድ አገልግሎቶች የሚገኘውን የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል።
👉የአካባቢው የዶሮ፣ የወተት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች ለግዙፉ አውሮፕላን ማረፊያና ለሆቴሎቹ ምርቶቻቸውን በስፋት የሚያቀርቡበት ሰፊ የገበያ እድልም ይፈጥርላቸዋል።
👉የማክሮ ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን በሀገር ውስጥ ምርት እድገት፣ በውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና በውጪ ምንዛሪም ማሳደግን ያስችላል፡፡
👉ማረፊያው በሚሊየን የሚቆጠሩ መንገደኞችን እና በሚሊየን የሚቆጠር ቶን ጭነት ማስተናገዱ በራሱ ለሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ምርት እድገት ቀጥተኛ እና ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታል።
👉ምቹ፣ ፈጣን እና ዘመናዊ የአየር ትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ መሠረተ ልማት መኖሩ ዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎችና ፋብሪካዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ዋነኛ ማበረታቻ ይሆናል።
👉ከአገልግሎቶች፣ ከነዳጅ ሽያጭ፣ ከትራንዚት ሆቴሎች እና ከቀረጥ ነፃ የንግድ ማዕከላት የሚገኘው ገቢ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በዘላቂነት ይቀርፋል።
👉የወጪ ንግድ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እድገት በማሳለጥ ረገድም የላቀ ሚና ይጫወታል፡፡ እንደ አበባ፣ ፍራፍሬ፣ አትክልትና ስጋ ያሉ በቀላሉ ሊበላሹ የሚችሉ የኢትዮጵያ እና የሌሎች ሀገራት ወጪ ምርቶች ሳይዘገዩ በጥራት ለዓለም ገበያ እንዲቀርቡ በማድረግ የገበሬውንና የላኪውን ገቢ ያሳድጋል።
👉በአውሮፕላን ማረፊያው አቅራቢያ እና በሀገሪቱ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያመርቷቸውን የጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ እና የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች በከፍተኛ ፍጥነት ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና እስያ ገበያዎች ለማጓጓዝ ምቹ የሎጂስቲክስ ሰንሰለት ይፈጥራል።
👉የአህጉሪቱ የንግድና የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ ዋና ማስተላለፊያ ማዕከል በመሆን የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ተሰሚነትም ያጠናክራል።