Fana: At a Speed of Life!

438 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ438 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል አለ ጉምሩክ ኮሚሽን።

ኮሚሽኑ ከሰኔ 19 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 422 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገቢና 16 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች የያዘው፡፡

ከተያዙት እቃዎች ውስጥ አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ አደንዛዥ እጾች እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሞያሌ እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡

በሌላ በኩል ከኮንትሮባንዱ ጋር በተያያዘ 26 ተጠርጣሪዎች እና 13 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.