Fana: At a Speed of Life!

ስፔን ከቤልጂዬም፣ ተጠባቂው ጨዋታ…

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጥምር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው በ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬም ቀጥሎ ይደረጋል፡፡

ምሽት 4 ሰዓት ላይ የአንድ ጊዜ የመድረኩ አሸናፊ ስፔን ከቤልጂዬም ጋር የምታደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ስፔን በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፖርቹጋልን እንዲሁም ተጋጣሚዋ ቤልጂዬም ደግሞ አዘጋጇን ሀገር አሜሪካን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡

የ2010 የመድረኩ ሻምፒዮን ስፔን በድጋሚ በመድረኩ ለመንገስ የምታደርገውን ጉዞ ለማጠናከር ወደ ሜዳ የምትገባ ይሆናል፡፡

በፈረንጆቹ 2018 ወርቃማ ትውልዷን ሳትጠቀም የቀረችው ቤልጂዬም በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ እስከ የት ድረስ ትጓዛለች የሚለው ተጠባቂ ነው፡፡

በስፔን ብሔራዊ ቡድን በኩል በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ 4 ግቦችን ያስቆጠረው ሚኬል ኦያርዛባል እና ወጣቱ ኮከብ ላሚን ያማል በዛሬው ጨዋታ ይጠበቃሉ፡፡

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች አሸናፊ በግማሽ ፍጻሜው ከፈረንሳይ ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.