ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ልምድ አጋርተውናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በምክክር ለምታረጋግጠው አንድነትና ዘላቂ የሰላም ጉዞ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ልምዳቸውን አጋርተዋል አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በታሪካዊው የሀገራዊ ምክክራችን ዋዜማ በምክክሩ ዙሪያ ከኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተወያይተናል ብለዋል፡፡
በውይይታችን ከዚህ ቀደም ካከናወኗቸው ተግባራት ጥበብ ለመቅሰም ችለናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በተለይም የቢያፍራን የሰላም ሂደት በመምራት ያካበቱትን ልምድ ማጋራታቸውን አመልክተዋል።
ይህም ኢትዮጵያ በምክክር ለምታረጋግጠው አንድነትና ዘላቂ የሰላም ጉዞ ላይ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ ኢትዮጵያ ለምታበረክቱት በዋጋ የማይተመን አስተዋጽኦ ሁልጊዜም የላቀ ምስጋናዋን ታቀርባለች ነው ያሉት፡፡