ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኳታር ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኳታር የቀድሞ አሚር ሼይኽ ሀማድ ቢን ካሊፋ አልታኒ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ለመግለጽ ኳታር ገብተዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ በኢትዮጵያ እና ኳታር መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ጠንካራ ወዳጅነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም በቀጣናው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጉልህ አሻራ ጥለው ያለፉትን መሪ የሚያከብር መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ ለኳታር ሕዝብና መንግሥት መጽናናትን ተመኝቷል፡፡