ማዕበልን ወደ ድል የመቀየር የዘመናት ታሪክ ያላት ብርቱ ሀገር
ኢትዮጵያ ማዕበልን ወደ ድል የመቀየር የዘመናት ታሪክ ያላት ብርቱ ሀገር ናት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን በመግለፅ፤ ሀገሪቱ በምትገኝበት ወሳኝ ምዕራፍ፣ ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራ መሰረት መጣል እንደምትችል አበክረው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ታሪክ የፈተናና የድል ጥምረት ነው። ሀገሪቱ በርካታ የውስጥና የውጭ ማዕበሎችን አስተናግዳለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) በሀገራዊ ምክክር የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ እንደተናገሩት ፤ ፈተናዎችን ማለፍ ለኢትዮጵያውያን አዲስ አይደለም።
ከችግር ውስጥ ትምህርት በመውሰድና በመደመር እሴት ጠንካራ ሆነው ብቅ ማለት የህዝቧ መገለጫ ነው።
ሀገራዊ ምክክር የሀገሪቱን ችግሮች በውይይት ለመፍታት ወሳኝ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሀገራዊ ምክክሩ የጋራ መግባባትን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ይገልጻሉ።
ልዩነቶችን በውይይት መፍታት እና የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ማዕበልን ወደ ድል ለመቀየር ቁልፍ መንገድ ነው።
“የጀመርናቸውን መልካም ዘሮች እንዘራለን፤ ነገር ግን ከሚያፈሩት ፍሬ እኛ ሳንሆን ትውልድ እንዲጠቀም እናደርጋለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይናገራሉ።
ይህ ማለት የዛሬው ጥረትና መስዋዕትነት ለነገው ትውልድ ብልጽግና መሰረት ነው።
ኢትዮጵያ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ እና በሌሎችም ሜጋ ፕሮጀክቶች እንዳሳየችው፣ ፈተናዎችን በማለፍ ለትውልድ የሚተርፍ ድልን መጎናጸፍ ልማዷ ነው።