Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ለመሥራት መላው ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥የኢትዮጵያውያን ክንድ ተባብሮ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ሌላ ታሪክ ለመስራት 5 ቀናት ብቻ ቀርተዋል ብለዋል።

ውድ የሀገሬ ልጆች በእነዚህ ቀናት አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ፣ በቁርጠኝነት እንድትነሱና በአንድነታችን የምናስመዘግበውን ድል እውን እናድርግ ሲሉም ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.