Fana: At a Speed of Life!

ለትግራይ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የህጋዊ እውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጠ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዲስ ስያሜ ህጋዊ እውቅና ለተሰጠው የትግራይ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ የምስክር ወረቀት ሰጥቷል። 

ባለሰልጣኑ የምስክር ወረቀቱን ለትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ያስረከበ ሲሆን፤ በክልሉ የህዝብ መረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ለሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎችና አመራሮች የአቅም ግንባታና ሌሎች ድጋፎች ማድረግ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡ 

የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የፓለቲካ ጉዳዮችና የህዝብ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ ረዳኢ ሃለፎም በዚሁ ወቅት፤ የባለአደራ አስተዳደሩ በክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትን ለማምጣት እንዲሁም የእድገትና የልማት ስራዎችን ለማፋጠን የሚያስችለውን የህዝብን የመረጃ ተደራሽነት ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

 ኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ድምፅ በመሆን አዎንታዊ ሚናውን በተገቢው እንዲወጣ በሚያደርገው ጥረት ባለስልጣኑ የሚያደርገውን እገዛና ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። 

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ በበኩላቸው÷ ተቋሙ በአዲስ ስያሜ ወደ ህዝብ ተደራሽ ለሆኑት የክልሉ ሚዲያዎች ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ 

በተለይም በሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሀን ህግ፣ በብሔራዊ ጥቅም፣ በሰላም ግንባታ፣ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ እንዲሁም በጋዜጠኝነት የሙያ ስነ ምግባር መዳበር አጋዥ የሆኑ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.