Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ ሐይቅ ተፋሰስ አካባቢ የሚታየውን የመሬት መሸርሸረ ለመከላከል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐዋሳሐይቅ ተፋሰስ አካባቢ የሚታየውን የመሬት መሸርሸር፣ የአፈርለምነት መጎዳት እና የአየር ንብረት መዛባት ችግሮችን በዘላቂነትለመቅረፍ ያለመ የችግኝ ተከላ በሐዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ ከኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት እና አጋሮቹ ጋር በመቀናጀት ነው የተካሄደው፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል እርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምህሩ ሞኬ፣ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፓስተር ተመስገን ግዛው እና ሌሎች ተሳትፈዋል፡፡

የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፓስተር ተመስገን ግዛው÷ ቤተ ክርስቲያኗ ከ280 ሺህ በላይ የተለያዩ የችግኝ ዓይነቶችን በማዘጋጀት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እየተሳተፈች ነው ብለዋል፡፡

የችግን ተከላ ንቅናቄው በሐዋሳ ሐይቅ ተፋሰስ አካባቢየሚታየውን የመሬትመሸርሸር፣ የአፈር ለምነት መጎዳት እና የአየር ንብረት መዛባት ችግሮችን በዘላቂነትለመቅረፍ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመልሶ ማልማት አጠቃላይ ስትራቴጂው በአምስት ዋናዋናየአካባቢጥበቃ ምሰሶዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን የተፋሰስ እና የአፈርጥበቃ፣ አፈርን በመንከባከብ የምግብዋስትናን ማረጋገጥ፣ ደንማልማትና አረንጓዴ ልማት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ከባቢ መፍጠር እንዲሁም ንጹሕ ኃይልና ዘመናዊ ማብሰያዎችን ማስፋፋትየሚሉትተጠቅሰዋል።

የአካባቢ ጥበቃ ተግባር ተራ ማህበራዊ አገልግሎት ሳይሆን የፈጣሪንቅዱስ አደራ የመወጣት መንፈሳዊ ኃላፊነት መሆኑም በችግኝ ተከላ ወቅት ተነስቷል፡፡

አቶ መምህሩ ሞኬ የሃይማኖት ተቋማት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርበመሳተፍ ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን አንስተዋል፡፡

እንደዚህ ያሉ ሃይማኖታዊ እሴቶችን ከአካባቢ ጥበቃ ሳይንስ ጋር ማቀናጀት የተበላሹ የስነ-ምህዳር ክፍሎችን በመፈወስ እና የደን ጭፍጨፋን በመግታትእንዲሁም እኩል የሰዎችን እና የተፈጥሮን ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ርምጃ መሆኑ ተናግረዋል።

ህብረተሰብ፣ የሃይማኖት አባቶች እና የልማትአጋሮች ችግኝ በመትከል፣ አፈርን በመንከባከብ እና ንጹሕ ኃይልን በመጠቀም የሐዋሳን ሐይቅ ከደቃቅ ደለልና የመድረቅ ስጋት እንዲታደጉጥሪቀርቧል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የ ሲዳማ ክልል የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት እና አጋሮቹ እና የአከባቢው ሕብረተሰብ ተሳትፈውበታል፡፡

በተካልኝ ሃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.