Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም ዶ/ር ጳውሎስ ቀንዓ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዶ/ር ጳውሎስ ቀንዓ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ሕክምና ትምህርት ክፍል መስራች ናቸው፡፡
ለሃገራቸው በርካታ ቀዳሚ ታሪኮችን ያስመዘገቡት ዶክተር ጳውሎስ ቀንኣ ከሃገር ወጥተው በውጭ ሃገር ለመስራት በርካታ እድሎች የነበሯቸው ቢሆንም፤ በቂ የሕክምና ዶክተሮች የሉንም በማለት ሃገራቸውን በታማኝነት አገልግለዋል፡፡
ከቤሩት አሜሪካዊ ዩኒቨርሲቲ (ሊባኖስ) የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የዓይን ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ጳውሎስ ቀንኣ፤ በ1956 ዓ.ም ወደ ሥራው ገበታ በመቀላቀል በሚኒሊክ ሁለተኛ ሆስፒታል ከእስራኤላዊው የዓይን ሐኪም ከዶክተር ዛጎራ ጋር ሥራ ጀመራቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ የዓይን ሕክምና ማኅበር ለማቋቋምም ዋናውን ሚና የተጫወቱት ዶ/ር ጳውሎስ ነበሩ።
በእርሳቸው የተጀመረው ይህ ክፍል በተጠናከረ መልኩ የቀጠለ ሲሆን እስካሁንም 118 የዓይን ሐኪሞች ተመርቀዋል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም ዶ/ር ጳውሎስ ቀንዓ በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.