ዓባይና ቀይ ባሕር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና ቀጣናዊ ትስስር የሚያረጋግጡ መሠረቶች ናቸው – ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓባይና ቀይ ባሕር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና ቀጣናዊ ትስስር የሚያረጋግጡ መሠረቶች ናቸው አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፡፡
ሚኒስትሩ ÷ ዓባይና ቀይ ባሕር የኢትዮጵያን እጣፈንታ ሲወስኑ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
የኢትዮጵያዊያን ሕልውና ከእነዚህ የውሀ አካላት ጋር ከፍተኛ ቁርኝነት እንዳለውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዓባይን እንዳታለማና እንዳትጠቀም የውጭ ሃይሎች በተለያዩ መንገዶች ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቁመው÷ በተመሳሳይ በሴራ ከቀይ ባሕር እንድትርቅ በማድረግ ኢትዮጵያውያን ብዙ ዋጋ ሲከፍሉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
በሕዳሴ ግድብ አማካኝነት ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ሲመኙት ከነበረው ህልማቸው መካከል አንዱን ማሳካት መቻሉንና ይህም በኢትዮጵያውያን ላይ ይደርስ የነበረውን ተጽዕኖ መስበር ያስቻለ ስኬት መሆኑን አንስተዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሀገሪቷ ላይ ሲደረጉ የቆዩ ደባዎችን ማስቀረት የቻለ የኢትዮጵያውያን ኩራት መገለጫ ፕሮጀክት እንደሆነ አውስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቀይ ባሕርን በተለያየ ሴራ እና ተንኮል እንድታጣ ከተደረገ በኋላ ይህንን ጉዳይ ማንሳት የማይፈቀድ እና ሌላ ስም የሚያሰጥ እንደነበር ነው የገለጹት፡፡
ኢትዮጵያ አሁን ላይ የባሕር በር ባለቤትነቷን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማግኘት አለብኝ ብላ ያነሳችው ጥያቄ ከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነት የታየበት መሆኑን ጠቁመዋል።
የቀይ ባሕር ጉዳይ የመንግሥት ወይም የአንድ ፖለቲካ ድርጅት ጉዳይ ሳይሆን ትውልድ ተሻጋሪ ስራ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ÷ዓባይና ቀይ ባሕር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና ቀጣናዊ ትስስር የሚያረጋግጡ መሠረቶች መሆናቸውን አንስተዋል።
እንዲሁም በቀይ ባሕር አቅራቢያ የሚታዩ ዓለም አቀፍ የጂኦ ፖለቲካዊ ውድድሮች እና የባሕር ላይ የደህንነት ስጋቶችን ማቃለል የሚያስችላት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያውያን በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ያሳዩትን አንድነት በቀይ ባሕር ላይ መድገም እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡