በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)በአሜሪካ ኦሪገን በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለት፡፡
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 ወርቅ፣ 3 ብር እና 1 ነሐስ በድምሩ 6 ሜዳልያዎችን በማግኘት ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን ማጠናቀቋ ይታወሳል።
ሻምፒዮናው በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ ሄይዋርድ ፊልድ ከሐምሌ 29 ቀን እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መካሄዱ አይዘነጋም፡፡