Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት በሙስና እና ህገወጥ ተግባራት ላይ እየወሰደ ያለው ርምጃ የሚበረታታ ነው – የጅማ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት በሙስና እና ህገወጥ ተግባራት ላይ እየወሰደ ያለው ርምጃ የሚበረታታ ነው አሉ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች፡፡
ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አስተያየታቸውን የሰጡት የጅማ ከተማ ነዋሪዎች በጥቂት ህገወጥ ግለሰቦች ምክንያት የልማት ስራዎች መጎዳት የለባቸውም ብለዋል፡፡
ሙስና እና ብልሹ አሰራር የሀገርን እድገት እንደሚጎዳ አንስተው፤ በህዝብና በመንግሥት መካከል ያለውን መተማመን ያላላል ነው ያሉት፡፡
በሌብነት የሚመዘበረው ሀብት ለትምህርት ቤቶች፣ ለጤና ተቋማትና ለሌሎች መሰረተ ልማቶች ቢውል ህዝብንና ሀገርን እንደሚጠቅም ገልጸዋል፡፡
መንግሥት በሙስና እና ህገወጥ ተግባራት ላይ እየወሰደ ያለው ርምጃ ሀገርን ከቁልቁለት የሚያድን፣ የልማት ስራዎችን የሚያፋጥንና ሀቀኛ ትውልድ መቅረጽ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ከሙስና የጸዳች ሀገር ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ የሁሉም አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ እንደ ሀገር የታየው አመርቂ ውጤት ሙስናን ከሀገር በማጥፋት ሊደገድም ይገባል ብለዋል።
ወርቅአፈራው ያለው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.