የወላይታ ሕዝብ ታሪክ ተመራማሪ አቶ አብራሃም ባቾሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወላይታ ሕዝብ ታሪክ ተመራማሪና የሶዶ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ የነበሩት አቶ አብራሃም ባቾሬ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ አብራሃም ባቾሬ በሕይወት ዘመናቸው በልማት፣ በአስተዳደር፣ በኮሙኒኬሽን፣ በባህል ጥናትና በማኅበረሰብ ዕርቅ ዘርፍ ለሀገርና ለሕዝብ ጉልህ ዐሻራቸውን አሳርፈዋል።
በኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ በዓለም አቀፉ የሕፃናት አቀፍ ድርጅት እና በዎላይታ ልማት ማኅበር ውስጥ እንዲሁም የሶዶ ከተማ ከንቲባ በመሆን አገልግለዋል።
አቶ አብራሃም የ”ጊፋታ” በዓል ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ እውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ የዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበራቸውም የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በአቶ አብራሃም ባቾሬ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጾ÷ ለቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ተመኝቷል።