Fana: At a Speed of Life!

የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የእግር ጉዞ እያደረጉ ነው።
የእግር ጉዞው “ንግግርን ወደ ተግባር” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ሲሆን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለማስፋፋት ዓላማ ያደረገ ነው።
በእግር ጉዞው የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የዓለም ጤና ድርጅት አመራሮች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እንዲሁም ሌሎች ታዋቂ አትሌቶች ተሳትፈዋል።
የጤና አመራሮቹ በጉዞው በመሳተፍ የአካል እንቅስቃሴ እንደ ስኳር በሽታ፣ የደም ግፊትና የልብ ሕመም ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል ያለውን ጠቀሜታ በተግባር ለማሳየት ያለመ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
የእግር ጉዞው ከአድዋ ድል መታሰቢያ ተነስቶ በከተማዋ የእግረኛ መንገድ በመከተል መስቀል አደባባይ ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ 76ኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን፣ በአፍሪካ የጤና ስልቶችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ያደርጋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.