Fana: At a Speed of Life!

የእስያ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእስያ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማምቷል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከእስያ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ዙ ዥያይ ጋር በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በተለይም ባንኩ በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ግንባታ ላይ የሚኖረውን ተሳትፎ እንዲሁም ሌሎች የትብብር አቅጣጫዎችን በተመለከተ መወያየታቸው ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር በኢነርጂ እና በአየር ንብረት ለውጥ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም ባንኩ ለኢትዮጵያ ተመጣጣኝ የፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በዚሁ ወቅት አቶ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ የተደረጉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የአፈጻጸም ሂደትን እና መንግሥት ገንብቶ ያጠናቀቃቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለኢኮኖሚው እያበረከቱ ያለውን አስተዋፅኦ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከእስያ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ዙ ዥያይ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ቀጣናውን በሀይል ልማት ለማስተሳሰር እያደረገች ያለውን ጥረት እና የመሪነት ሚና አድንቀዋል፡፡
የእስያ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ የሚገነቡ የመሰረተ ልማቶችን በፋይናንስ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.