Fana: At a Speed of Life!

አብሮነትንና አንድነትን በማጠናከር ለወገን አለኝታነትን ማሳየት ይገባል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አብሮነትንና አንድነትን በማጠናከር ለወገን አለኝታነትን ማሳየት ይገባል አሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ ለአረጋውያን ማዕድ አጋርተዋል።
በህይወት ፋና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኝተው ህሙማንንና የወለዱ እናቶችን በመጠየቅ ማዕድ ያጋሩት ርዕሰ መስተዳደሩ በተጨማሪም የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
እንዲሁም የኅብር ቀንን በማስመልከት በአብረሃ በሃታ አረጋውያን መርጃ ማዕከል በመገኘት በማዕከሉ የሚገኙ አረጋውያንን በመጠየቅ ማዕድ አጋርተዋል።
አቶ ኦርዲን በድሪ ስንተባበር፣ ስንተዛዘንና ስንረዳዳ ደስታን አብሮ ማሳለፍና ችግሮችን በቀላሉ መሻገር እንችላለን ብለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.