Fana: At a Speed of Life!

‎በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 592 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ‎

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 592 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

‎ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገ 9 ዙር በረራ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት ዜጎች መካከል 34ቱ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

‎ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማቀላቀል እየተሰራ ይገኛል፡፡

‎መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ103 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.