የተባበሩት መንግሥታት ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች መቐለ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ልዑካን፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት መቐለ ከተማ ገብተዋል፡፡
ልዑካኑ አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች እና የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ልዑካን ከዛሬ ሕዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በመቐለ ከተማ ያካሂዳሉ።
ልዑካኑ ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ከሐይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሰብዓዊ ዕርዳታ፣ ተፈናቃዮች፣ የዲዲአር (የትጥቅ የማስፈታት፣ የዲሞቢላይዜሽን እና የመልሶ ማቋቋም) ሒደት እንዲሁም የክልሉ ሰላም ጉዳይ ውይይት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው።
በግዛቸው ግርማዬ