Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸኃፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የመስቀል በዓል በተግባር የተገለጠ ፍቅር፣ የመታመን እና የትጋት ሽልማት ምልክት ነው ብለዋል።

የመስቀል በዓል ከታሪካዊና መንፈሳዊ ፋይዳው ባሻገር ሕዝባችን በአብሮነት፣ በፍቅርና በሰላም እንዲኖር ያስቻለ ታላቅ ሀገራዊና ሃይማኖታዊ እሴት መሆኑን አውስተዋል፡፡

 

በዓሉ በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ድልን የተጎናፀፍንበት፣ ሰላም የተሰበከበት እንዲሁም እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ወደር የማይገኝለት ፍቅር በተግባር ያየንበት ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

የመስቀልና የደመራ በዓል ኢትዮጵያውያን ዘር፣ ጎሳ፣ ቋንቋ እና የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድባቸው በአንድነት የሚያሰባስብ ታላቅ የማኅበራዊ ትስስር መሰረትም ሆኖ ለዘመናት እያገለገለ እንደሚገኝም አስታውሰዋል፡፡

በዓሉ የኢትዮጵያን ማኅበራዊ መስተጋብር፣ እንግዳ ተቀባይነትና ባህላዊ እሴቶች ለዓለም የሚያስተዋውቅ ታላቅ ቅርስ በመሆኑ የጥላቻና የግጭት መንፈስ ተወግዶ የይቅርታና የሰላም አየር እንዲሰፍን በፀሎት በመትጋት እንዲሁም ስለሠላም በማስተማር ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.