Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሠራዊት የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተመራ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መርቷል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ቁጥር 1286/2015 እንዲሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ይገኝበታል፡፡

መከላከያ ሠራዊት በኢፌዴሪ ህገ መንግሥት አንቀጽ 87 ድንጋጌዎች መሰረት የተሰጡትን ሀገራዊ ተልዕኮዎች በህግ አግባብ ለመፈፀም እንዲችል የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡

በዚህም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀረበለት ረቂቅ አዋጅ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.