Fana: At a Speed of Life!

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ነገን የሚሰሩ ታዳጊዎችን የሚያፈሩ መሰረተ ልማቶች እየተገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳይንስና ቴክኖሎጂ የበለጸገ ትውልድና ነገን የሚሰሩ ታዳጊዎችን ማፍራት የሚያስችል መሰረተ ልማቶች እየተገነቡ ነው አሉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ።

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ ትምህርት ቤትን መርቀው ከፍተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የበለጸገ ትውልድና ነገን የሚሰሩ ታዳጊዎችን ማፍራት የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች እየተገነቡ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሮቦቲክስ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ፋና ወጊ ሆኖ እየሰራ እንደሚገኝ እንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የታዳጊዎችን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎት በማጎልበት የዩኒቨርሲቲውንና የማህበረሰቡን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ በ2019 የትምህርት ዘመን ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 8ኛ ክፍል ከ1 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተምርም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.