Fana: At a Speed of Life!

ህገወጡ ቡድን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለተጨማሪ ጦርነት ለመዘጋጀት ሲጠቀምበት ነበር – አብረሃም በላይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ህገወጡ የህወሓት ቡድን የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ለተጨማሪ ጦርነት ራሱን ለማዘጋጀት እንደ ጊዜ መግዣ ሲጠቀምበት ነበር አሉ አብረሃም በላይ (ዶ/ር)።
አብረሃም በላይ (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ቆይታ፤ የፌደራል መንግሥት ለክልሉ ህዝብ እረፍት ለመስጠት በማሰብ የሰላም ስምምነቱን መፈራረሙን አንስተዋል፡፡
ስምምነቱ ዘላቂ ሰላም ማምጣትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ግጭት እንዲቆምና በክልሉ ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡
ሆኖም ህገወጡ ቡድን ተፈናቃዮችን ለፖለቲካ ዓላማው ለመጠቀም ባደረገው የማሰናከል ተግባር ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ሙሉ በሙሉ ወደቀያቸው ለመመለስ የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት ሳይሳካ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡
ህገወጡ ቡድን ስምምነቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም መንግሥት ለትግራይ ክልል የመደበውን በጀት ለልማት ሳይሆን ታጣቂዎችን ለማሰልጠንና ለጦር መሳሪያ ግዥ ሲያውል ቆይቷል ነው ያሉት፡፡
የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል የተደረሰውን ስምምነት በግልጽ በመጣስ ለክልሉና ለሀገሪቱ አደጋ የሆኑ ተግባራት ላይ ሲሳተፍ ቆይቷል ብለዋል።
በተጨማሪም ሌሎች የጥፋት ኃይሎችን በማስተባበር በሀገር ሉዓላዊነት ላይ አደጋ ደቅኖ መቆየቱንም ነው የገለጹት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.