Fana: At a Speed of Life!

የሆራ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሆራ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ከተማ መልካ ሀርሰዴ በአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች ምርቃት በድምቀት መከበር ጀምሯል፡፡
በዓሉ “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል፡፡
የሆራ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች የምርቃት ስነስርዓት የተጀመረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በሀርሰዴ መልካ የኢሬፈና (የምስጋና) ስነስርዓት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ሁሉን ነገር ለፈጠረ አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን ፈጣሪን የሚለመንበት በዓል ነው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.