ጉባዔው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) በድጋሚ በመመረጣቸው የተሰማውን ደስታ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ መመረጣቸውን አስመልክቶ የደስታ እና የአጋርነት መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ጉባዔው አዲሱ የመንግሥት ምስረታ በተሳካ ሁኔታ በመካሄዱና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በድጋሜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው የተሰማውን ልባዊ ደስታ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው ደብዳቤ ገልጿል፡፡
አዲስ ከተመሰረተው መንግሥት ጋር በመተባበር የጋራ በሆኑ አጀንዳዎች ማለትም በሰላም ግንባታ ፣ግጭትን በመከላከልና በመፍታት፣የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከርና መሰል ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥቷል።