Fana: At a Speed of Life!

የካቢኔው ሹመት ህብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን የሚያንፀባርቅ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የካቢኔው ሹመት ህብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን የሚያንፀባርቅ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡
በዚህም በመደበኛ ስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን ዝርዝር አቅርበው በምክር ቤቱ ፀድቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ÷ የመመዘኛ መስፈርቱ ከዕጩዎቹ የትምህርት ዝግጅት እና የመፈጸም አቅም በማስከተል ፆታን እምነትን እና ብሔርን ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያን መሻት እንዲሁም የዜጎችን ጥቅም ለማስፈጸም በሚደረገው ጉዞ እነዚህን ጉዳዮች ታሳቢ ካላደረግን ህብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን ማንፀባረቅ አንችልም ብለዋል፡፡
የተሾሙት የካቢኔ አባላት ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የማይወጡ ከሆነ እርምጃ እንደሚወሰድም አረጋግጠዋል፡፡
በመደበኛ ስብሰባው ላይ የተሾሙት የመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ፊት በይፋ ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
በምህረት ደምሴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.