ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የካቢኔ ዕጩዎችን ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የሰጡት ምላሽና ማብራሪያ:- On Oct 8, 2026 208 ጾታን ታሳቢ አድርገን ስንሠራ ጥሩ ይመጣልንና የብሔር ጉዳይ ዕዳ ይሆናል፤ የብሔር ጉዳይን አሟልተን ስንሠራ የእምነት ጉዳይ ችግር ይሆናል፤ ሁሉን ያሟላ የለም፣ ፆታም እምነትም ብሔርም ያሟላ እንዲሁ በዋዛ አይገኝም። ትምህርትና ልምድ ብቻም አይደለም፡፡ ትግራይ ክልልን ብንወስድ ባለፉት ዓመታት የካቢኔ አባል ሆነው ያገለገሉ አንድ ሰው ነበሩ፤ ባሁኑ የትግራይ ክልል ሁለት የካቢኔ አባላት አላቸው፡፡ ሁለት መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ወንድና ሴት፣ ክርስቲያንና ኢስላምም ናቸው፡፡ ብዙ ሒሳቦች ተሰርተው እንደቀረቡ ከግምት እንድታስገቡ ነው፡፡ በባለፈው ሹመት የአማራና ኦሮሞ ኮታ ይሰፋ ነበር አሁን ሌሎቹን ለማካተት ሲባል የአማራና የኦሮሞ ኮታ እንዲቀንስ ተደርጓል፤ ሀረሪ በሚኒስትርነት ደረጃ የቀረበው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ሁሉም ጉዳዮች ታሳቢ የተደረጉ ቢሆንም አሁንም ግን 100 ፐርሰንት የተሟላ ላይሆን ይችላል፡፡ ሰው የሰራው ሥራ ሙሉ መሆን አይችልም፤ ሰው ሰው ስለሆነ፣ እያየን እናንተም እያያችሁ የጎደለ፣ የሚታረምና የሚስተካከል ነገር ካለ ከ24 ሰዓት በኋላም ቢሆን ተጨባጭ ማስረጃ ካገኘን መቀየር እንችላለን፡፡ ሹመቱ ቋሚ አይደለም፤ በሥራና በውጤት ብቻ የሚቀጥል ጉዳይ ነው፡፡ በሴቶች ጉዳይ እኛ ለዓለም ምሳሌ ስለሆንን ሌሎች ሀገራት ከእኛ መማር አለባቸው፡፡ ከ22 ሚኒስትሮች 9 ሴት ሚኒስትር ያደረገ አንድ ሀገር መጥራት አይቻልም፡፡ አደግኩ፣ ሰለጠንኩ በለጸግኩ የሚል፣ ስለሴቶች መብት ከኛ በላይ የሚያወራም ቢሆን ሁለት ሶስት ሰው ቢገኝ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ጥሩ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ሴት ስለተሆነ ብቻ አንሾምም፤ ባለፉት ጊዜ ሴት ሴት ብቻ በሚል ያመጣነው ጉዳይ በአስተምህሮ ደረጃ የተሳካ አልነበረም፡፡ መሥራት የምትችል የሚለው ታሳቢ ተደርጓል፡፡ 9 ሚኒስትር የሚያኮራ ውሳኔ ተደርጎ መወሰድ አለበት፡፡ #የመደመር_መንግሥት በቤተልሔም ግርማ 208 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint