Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት ለህዝብ ቃል የገባውን በተጨባጭ ውጤት ለመመለስ በትኩረት ይሰራል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት ለህዝብ ቃል የገባውን ሥራዎች በተጨባጭ ውጤት ለመመለስ በትኩረት ይሰራል አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።

በሀረሪ ክልል የ2019 ዓ.ም አንደኛ ሩብ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሉት÷ የግምገማ መድረኩ እንደ መንግሥት ለህዝብ ቃል የገባናቸው ሥራዎች የማስፈፀም ሂደት የሚገመገምበት ነው።

ከአዲሱ መንግሥት ህዝቡ አዲስ ተስፋ ሰንቆ የሚጠብቃቸው ሥራዎች መኖራቸውን ገልጸው ህዝብ የጣለው ተስፋና አደራ ለአመራሩ ከፍተኛ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የዛሬው መድረክ በበጀት ዓመቱ ከተቀመጡ የዕቅድ አፈፃፀም ሥራዎች አንፃር ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሆነም ጠቁመዋል።

በአዲሱ መንግሥት የሥራ ዘመን ከዚህ ቀደም የነበሩ ድክመቶችን በማረምና ጥንካሬን በማስፋት በከፍተኛ ኃላፊነት ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ የበጀት ዓመቱ አንደኛ ሩብ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ የዕቅድ አፈፃፀም ሥራዎች ተገምግመው ቀጣይ አቅጣጫም ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አፈጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድን ጨምሮ የተቋማት እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.