Fana: At a Speed of Life!

“ኤርትራ ለወጣቶቿ ሲኦል ሆናለች!”

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ35 ዓመታት ሀገሪቱን የግል ንብረቱ አድርጎ የያዘው የኢሳያስ አፈወርቂ አምባገነናዊ ሥርዓት ኤርትራን ምድራዊ ሲኦል አድርጓታል።

ልማት፣ ዴሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ ኢንቨስትመንት የሚባሉ የሀገር እድገትና ህልውና መሠረት የሆኑ ጉዳዮች በኤርትራውያን ዘንድ የማይታወቁ እንዲሆኑ ተደርጓል።

የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል የዲፕሎማሲ ኃላፊ ዮኤል ዮሐንስ÷ ኤርትራን ከዓለም ነጥሎ የግል ርስቱ ያደረገው የኢሳያስ ሥርዓት የኤርትራውያን ዋነኛ ጠላት መሆኑን ያነሳሉ።

ሠላም ሠፍኖ ሕዝቡ ማህበራዊ እረፍት ካገኘ በኢትዮጵያ እና በሌሎች ጎረቤት ሀገራት የሚመለከተውን የልማትና የእድገት ጥያቄ ስለሚያነሳ ዘላቂ የደኅንነት ስጋት ውስጥ እንዲቀመጥ እንደሚያደርግም አስረድተዋል።

ለዚህም በሀገሪቱ ከሚያደርገው መንግሥታዊ ሽብር ባለፈ ለቀጣናው ሀገራትም የአለመረጋጋት መንስኤ ሆኖ ነው ያሉት፡፡

የኤርትራ ወጣቶች ከአምባገነናዊው ሥርዓት በመሸሽ እየተሰደዱ መሆኑን ጠቁመው÷ ኢትዮጵያም የኤርትራ ሕዝብ የክፉ ቀን መጠለያ ሆና መቀጠሏን ገልፀዋል።

የሀገሪቱን ኢኮኖሚ፣ ዲፕሎማሲና ገጽታ በጥቁር መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ያደረገው የኢሳያስ ሥርዓት እስካልተወገደ በኤርትራ ዘላቂ ሠላምና እድገት እንደማይታሰብ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በመላው ዓለም የሚገኙ ኤርትራውያን ሀገር አልባ ያደረጋቸውን አምባገነናዊውን ሥርዓት ለመታገል መነሳት እንደሚገባቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

በሞሊቶ ኤልያስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.