Fana: At a Speed of Life!

የውቅሮ ነዋሪዎች ከተማዋን በተለያዩ አደረጃጀት የሚያገለግሉ አመራሮችን መረጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውቅሮ ከተማ ነዋሪዎች ከተማዋን በተለያዩ አደረጃጀት የሚያገለግሉ አመራሮችን መርጠዋል፡፡
‎የፕሪቶሪያን ስምምነት ተከትሎ የተመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳዳር በሐይል በማፍረስ ሥርዓት አልበኝነትን ያነገሰው ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ከትግራይ ሕዝብ ጫንቃ ተወግዷል።
‎
የትግራይን ሕዝብ ብሎም ሀገርን ለብዙ ኪሳራ የዳረገው ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ከመላው የትግራይ አከባቢዎች መወገዱን ተከትሎ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን እና መሰረት ልማቶችን አውድሟል።
‎
‎ሕብረተሰቡ መደኛ የመንግሥት አገልግሎት እንዲያገኝና ሰላምና መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ በቀጥታ መሪዎችን እንዲመርጥ እየተደረገ ይገኛል።
‎በዚህ መሰረት የውቅሮ ከተማ ነዋሪዎች መምህር ገብረመስቀል ኪዳኑን የከተማዋ ከንቲባ አድርገው ሲመርጡ ሌሎች አራት የሥራ አስፈፃሚ አባላትን መርጧል።
‎
‎እነዚህ የተመረጡ አስተዳዳሪዎች በትግራይ መደበኛ ምርጫ እስከሚካሄድ ከ6 እስከ 8 ወራት ድረስ የሚቆዩ ናቸው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.