Fana: At a Speed of Life!

አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በኒውክሊየር ኃይል ትብብር ዙሪያ ከሩሲያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ከሩሲያ ፌዴሬሽን አምባሳደር ዬቭጌኒ ቴሬኪን ጋር በኒውክሊየር ኃይል ትብብር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር የተፈረመውን ስትራቴጂካዊ የትብብር ፍኖተ ካርታ ወደ ተግባር ስለሚሸጋገርበት ሁኔታ መክረዋል።

ውይይቱ በኒውክሊየር ኃይል ዘርፍ ለሚደረገው ትብብር የሚያስፈልጉ የሕግ ማዕቀፎችንና መሠረተ ልማቶችን በማሟላት፣ እንዲሁም የሀገር ውስጥ የሰው ኃይልን አቅም በመገንባት የኢትዮጵያን የኢነርጂ አማራጮች ለማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

ከዚህም ባሻገር፣ የኒውክሊየር ቴክኖሎጂን በዘመናዊ ሕክምናና በግብርና ዘርፎች ለሰላማዊ ዓላማ በመጠቀም፣ ዓለም አቀፍ የደህንነት መስፈርቶችን በማሟላት የቴክኖሎጂውን ጥቅም ለሀገራዊ ልማት ለማዋል ያለውን እድል በውይይቱ መዳሰሳቸው ተገልጿል።

ይህ ስትራቴጂካዊ ትብብር በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ዘመናት የተሻገረ ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ አዲስ የቴክኖሎጂና የልማት ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን የኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.