በዓላማ ጽናት የታነጸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ለአንድ ሀገር ህልውና ሉዓላዊነቷን የሚጠብቅ፣ ሰላሟን የሚያስከብርና የሕዝቧን ደህንነት የሚያረጋግጥ ብቁ ተቋም መኖሩ የግድ ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትም የሀገሪቱን ነጻነት፣ ክብርና የህዝቧን ደህንነት በጽናት ከሚጠብቁ ቁልፍ ተቋማት አንዱ ነው።
የኢትዮጵያውያንን የጀግንነትና የአይበገሬነት ታሪክ ከዘመናዊ ወታደራዊ እውቀት፣ ቴክኖሎጂና ሙያዊ ብቃት ጋር በማጣመር ሠራዊቱ ለዘመኑ የደህንነት ፈተናዎች የተዘጋጀ ብቁ እና ንቁ ኃይል ነው፡፡
ሠራዊቱ ጠላትን በዘመናዊ የውጊያ ስልት እና በፍጥነት መመከት የሚችል በምድር፣ በአየር፣ በባህር እና በሳይበር ዘርፎች ዝግጁነት ያለው በተቀናጀ አሰራርና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የዳበረ ክህሎት ያለው የሀገር ሰላምና ሉዓላዊነት መከታ ነው፡፡
በብቃት፣ በዲሲፕሊንና በተገቢ ዝግጁነት የተገነባ መከላከያ ሠራዊት ግጭትን ለመከላከል፣ የድንበር ደህንነትን ለማረጋገጥና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት መጠበቅ የሚችል ነው፡፡
የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ በማህበረሰባዊ ድጋፍ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ፣ በግብርና፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እንዲሁም በሌሎች ሀገራዊ የልማት ጥረቶች የሕዝብ አጋርነቱን አስመስክሯል፡፡
ይህም ሠራዊቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ የህዝብ ደህንነትን እና ሀገራዊ ጥቅም ያስቀደመ በሕገ መንግሥታዊ ግዴታ በሙያዊ ሥነ-ምግባር የሚመራ ተቋም መሆኑን ያሳያል።
በአፍሪካ ቀንድና በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች የሚኖረውም ተሳትፎ ለቀጣናዊ ትብብርና ለጋራ ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጥ ነው።
የሠራዊት ጥንካሬ በመሳሪያና በወታደራዊ ቁመና ብቻ ሳይሆን፤ በሕዝብ እምነት፣ በተጠያቂነትና ሙያዊ ስነ-ምግባርም የሚለካ እንደመሆኑ ሠራዊቱ ከሕዝብ ጋር ያለው መተማመን እና ትስስር ሲያጠናክር ለሀገር ሰላምና መረጋጋት ያለው አስተዋጽኦ ይጎለብታል።
ይህም የሀገሪቱን የልማትና የብልጽግና ርዕይ ማሳካት፣ ሰላምን ማስጠበቅና ሉዓላዊነትን ለማስከበር የሁሉም ዜጎችና ተቋማት የጋራ ኃላፊነት እንዲሆን ያደርጋል።
ጠንካራ መከላከያ ሠራዊት ለሰላም፣ ለሉዓላዊነትና ለሀገራዊ ልማት ስኬት መሰረት እንደመሆኑ፤ የመከላከያ ሠራዊቱ ሙያዊ ብቃት፣ የሕዝብ ድጋፍና አንድነት መጠናከር ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ዘላቂ ደህንነት እና ልማት መከታ ነው፡፡
በምሕረት ደምሴ