Fana: At a Speed of Life!

ለዓለም የተገለጠው የኢትዮጵያ የቱሪዝም መስህብ – የተፅዕኖ ፈጣሪው ካሊድ መደነቅ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በባህልና በተፈጥሮ ውበት የበለፀገች የጎብኚዎች መዳረሻ ናት። የሕዝቧ ብዝሃነት፣ ባህልና የአኗኗር ዘይቤም አገሪቱን የብዙዎችን ቀልብ የምትስብ ታላቅ ምድር ያደርጋታል።
ወደ ምድረ ቀደምቷ ሀገር በተለያዩ ጊዜያት ለጉብኝት የሚመጡ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የሚሰጧቸው አስተያየቶችም በኢትዮጵያ አስደማሚ መልክዓ ምድር፤ ተስማሚ የአየር ንብረት፤ አስደናቂ ባህሎችና እንግዳ ተቀባይነት መደመማቸውን ይመሰክራሉ፡፡
በርካታ ጎብኝዎች የተደነቁባቸውንና አይረሴ ቆይታቸውን ጨምሮ ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገች እና እየተለወጠች መሆኗን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው የቪዲዮ፣ ፎቶና ጽሁፍ መረጃዎችን ያጋራሉ።
ሀገሪቱ ባከናወነቻቸው ሰፋፊ የከተማ የኮሪደር ልማት ስራዎች በቀደመው ጊዜ የነበራትን ጎስቋላ መልክ ቀይራ አስደናቂ ገጽታዋን ለዓለም እየገለጸች ነው።
የአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ መገለጫ የሆኑት ንጹህና ሰፋፊ መንገዶችን የወንዝ ዳርቻ ፓርኮች እና አረንጓዴ ስፍራዎችን እንዲሁም ታሪካዊ ቦታዎች ለዜጎች ምቹና ማራኪ የመኖሪያ ሥፍራ እንዲሁም ለውጪ ሀገራት ጎብኚዎች ድንቅ የመስህብ ማዕከል ሆናለች፡፡
በቅርቡም የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪው ካሊድ አል አምሪ፣ 9 ሚሊየን ለሚጠጉ ተከታዮቹ የኢትዮጵያን የተለያዩ አካባቢዎች አስጎብኝቷል፡፡
በአዲስ አበባ በነበረው ቆይታ የዓድዋ ድል መታሰቢያን እና ሙዚየምን ጎብኝቶ የኢትዮጵያን ነጻነት እና የህዝቦቿን ጀግንነት ለዓለም ተርኳል።
በዓድዋ ጦርነት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ጥሪያቸውን ሰምቶ ከየሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ሰራዊት በማስተባበር የሀገሪቱን ሉዓላዊነቷን ሊዳፈር የመጣውን የጣሊያን ጦር በድል አድራጊነት መመከታቸውን ተናጋሯል።
ይህም በጀግኖች ልጆቸዋ መስዕዋትነት ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ስር ያልወደቀች የአፍሪካ ሀገር እንድትሆን አድርጓታል ሲል አድናቆቱን ለተከታታዮቹ አጋርቷል።
ድሉ በሀገር ፍቅር በህዝብ አንድነት እና የአላማ ጽናት የተገኘ ነው ያለው ካሊድ፣ የዓድዋ ድል በአንድነት የመቆም የመጽናት እና የአሸናፊነት ማሳያ መሆኑን ማረጋገጫ ስለመሆኑ በመደነቅ ድሉን አወድሷል፡፡
የተጓዘባቸውን የአለም ሀገራት ባህላዊ ምግቦች እና መጠጦችን በመሞከር ለተከታዮቹ የሚያጋራው ካሊድ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ እና መጠጦች በተለይም ጥሬ ስጋ፣ ክትፎ እና ብርዝ እጅግ አስደናቂ ጣዕም ያላቸው ሆነው አግኝቷቸዋል፡፡
በኢትዮዮያ ቆይታው በታሪካዊ፣ ሐይማኖታዊ እና የባህል እሴቶቿ በዓለም የምትታወቀዋን የሀረርን የተለያዩ የመስብ ስፍራዎችንም ጎብኝቷል፡:፡
በተለይም ወደ ከተማዋ የሚያቀኑ ቱሪስቶች በሚያዘወትሩት የጅብ እና ጭልፊት መመገብ ትርዒት ላይ የታደመው ካሊድ ይህ ለእርሱ አዲስ ተሞክሮ መሆኑን እና ቆይታውን እጅግ እንዲወደው እንዳደረገው ምስክርነት ሰጥቷል፡፡
ውብ እና ታሪካዊ ቦታዎችን መጎብኘት ለሚፈልጉ አለም ዓቀፍ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን በመዳረሻ ዝርዝራቸው ውስጥ እንዲያካትቱ ምክር ሰጥቷል።
የመደመር መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት በሰራቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች ከዘርፉ የሚጠበቀውን ገቢ እንድታገኝ ታላቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው፡፡
በምህረት ደምሴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.