Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ፤ አርሰናል ከኤቨርተን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ እንዲሁም አርሰናል ከኤቨርተን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

የዛሬ መርሐ ግብር በቪላ ፓርክ የሊጉ መሪ ማንቼስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ ቀን 8 ሰዓት ከ30 በሚያደርጉት ጨዋታ ጅማሮውን ያደርጋል፡፡

11 ሰዓት ላይ ደግሞ አርሰናል በሜዳው ኤቨርተንን ሲያስተናገድ በተመሳሳይ ሰዓት ኮቨንትሪ ከፉልሃም ጋር ጨዋታቸውን ያደረጋሉ፡፡

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ደግሞ በለንደን ደርቢ ቼልሲ በሜዳው ቶተንሃም ሆትሰፐርን ያስተናግዳል፡፡

ሊጉን ማንቼስተር ሲቲ በ21 ነጥብ ሲመራ አርሰናል በ18፣ ብራይተን በ16 እና ቼልሲ በ13 ነጥብ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

የኮከብ ጎል አስቆጣሪነት ፉክክሩን ሃላንድ ከማንቼስተር ሲቲ በ8፣ ዣኦ ፔድሮ ከቼልሲ በ5፣ አሊክሳንደር አይዛክ ከሊቨርፑል በ5 እንዲሁም ዶሚኒክ ካልቨርት ሉዊን ከሊድስ በ4 ጎል ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.